የልብ ህሙማን ፈጣን የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲያገኙ ከመንግስትና ሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው – የኢትዮጵያ ልብ ማህበር

አዲስ አበባ መጋቢት 15/2015 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ለማግኘት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ከ10ሺህ በላይ ህሙማን ፈጣን የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲያገኙ ከመንግስት እና ሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ልብ ማህበር ገለፀ፡፡

ማህበሩ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የልብ ህክምና አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

 

የምክክሩ ዓላማ ከባለድርሻ አካላት ጋር የልብ ህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ለመምከር መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ልብ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ እንዳለ ገብሬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በኢትዮጵያ የልብ ህክምና አገልግሎት ተደራሽነት ከፍላጎት አንጻር ዝቅተኛ ነው፡፡

የስርጭቱ ሁኔታም በታዳጊ አገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን ገልጸው፤ እንደ አገር የልብ ህክምና የሚሰጡ የመንግስትና የግል ተቋማት ከአስር እንደማይበልጡ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ10ሺህ በላይ የልብ ህሙማን ህክምናውን ለማግኘት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች በፍጥነት ቀዶ ጥገና እንዲያገኙ ከመንግስት፣ ከግል ተቋማት እና ከባለሃብቶች ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢሊባቡር ቡኖ በበኩላቸው፤ በአገር ውስጥ የልብ ህክምና የሚሰጡ ተቋማት በቂ ባለመሆናቸው ዜጎች ለስቃይ እየተዳረጉ ነው ብለዋል፡፡

ህክምናው በብዛት በውጪ አገራት የሚሰጥ እና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑም የበሽታውን አሳሳቢነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲጨምር ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ለመቆጣጠር የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ለልብ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን ማሟላት እና የዘርፉን የህክምና ተቋማት ማስፋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል ስለመሆናቸውም ጠቁመዋል፡፡

ዜጎች እንደ ልብ በሽታ እና መሰል ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡

 

Donate
01308634568800 አዋሽ ባንክ 1000437345337 ንግድ ባንክ
0987777879 ቴሌ ብር
payment for membership
የታካሚ 250
የነርስ300
የፌሎ500
ሰብ ስፔሻሊስት 1000
የተቋም (የድርጅት)20,000 በዓመት
የክብር 25,000 በዓመት

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top